በመስፋፋት ላይ ያሉ የአገሪቱ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች እና ኢንዱስትሪዎች በኮምፒውተር ላይ የተመሰረቱ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ለጥቃት በመጋለጣቸው እና ወደፊት ይበልጥ ተጋላጭ እየሆኑ የሚሄዱ በመሆናቸው ደህንነታቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኮምፒውተሮች አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትስስር ምክንያት የተፈጠረው የሳይበር ምህዳር ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት እንዳይሆን መከላከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ኢንፎርሜሽን ቁልፍ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሃብት በመሆኑ ለደህንነቱ ጥበቃ ማድረግ ወሳኝ ሆኖ በመገኘቱ፤
ብሔራዊ ጥቅምን እና የዜጎችን መብት ለማረጋገጥ ኢንፎርሜሽን እና ኮምፒውተርን መሰረት ያደረጉ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ደህንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ሆኖ በመገኘቱ፤
ኢንፎርሜሽን እና ኮምፒውተርን መሰረት ያደረገ ቁልፍ መሰረተ ልማት ደህንነት ለመጠበቅ የሚደረገውን አገራዊ ጥረት የሚያቀናጅ እና ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ እና ስትራቴጂን በብቃት ማስፈጸም የሚችል ጠንካራ ተቋም መገንባት በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•