በአገልግሎት ላይ

የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች ከመቀበልና ከማስመረቅ ባለፈ፤ ከጥራትና ብቃት እንዲሁም ሀገሪቱ ቅድሚያ በምትሰጠው ዘርፍ በቂና ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት በኩል ውስንነቶች ያሉ በመሆኑ፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህግና ስርዓትን ተከትለው ተልዕኳቸውን በስኬት በመወጣት መንግስትና ህዝብ የሚጠብቅባቸውን ውጤት ማስገኘት እንዳይችሉ ዘርፉን የሚመራው ህግ የነበረው የይዘት ክፍተትና ይህም ያስከተለው የአፈጻጸም ጉድለት አንዱ የዘርፉ ችግር ሆኖ በመገኘቱ፤

የከፍተኛ ትምህርት ስርዓትና ተቋማት የትምህርት አግባብነትና ጥራትን ያረጋገጡ እንዲሆኑ፤ ተቋማት የትምህርትና ስልጠና፣ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት መስጫ ማዕከል እንዲሆኑ፤ ሀገሪቱ ቅድሚያ ለምትሰጣቸው ዘርፎችና ችግሮች ቅድሚያ የሚሰጡ እና ተቋማዊ አስተዳደሩ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ፍትሐዊነት የሰፈነበት ማድረግ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ከሀገራችን የዕድገትና ተቋማቱ ሊኖራቸው ከሚገባ ቁመና ጋር የተጣጣመ ለማድረግና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል፤ በዕውቀት፣ በክህሎት እናበስነ-ምግባር የዳበሩ ብቁ ዜጎች ማፍራት፤ በህግና ስርዓትን ማዕቀፍ ውስጥ ተጠያቂነትንና ኃላፊነትን በአረጋገጠ ሁኔታ ተቋማዊ እና አካዳሚክ ነጻነታቸው ተጠብቆ፤ ተልዕኳቸውን መወጣት እንዲችሉ ለማድረግ ነባሩን ህግ በማሻሻል አዲስ ህግ ማውጣት በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፊዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 55(1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡-

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1152/2011
ቀን: ነሐሴ 6፥ 2011 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

569/2017

የካቲት 26÷ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 561/2016

ህዳር 23፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 458/2012

መስከረም 23 ፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ