በአገልግሎት ላይ

የሚስጥራዊ መረጃዎች ምደባ እና ጥበቃ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመመደብና ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ባለመዘርጋቱ በብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየተፈጠረ በመሆኑ፤ የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመመደብ፣ ደረጃቸውን ለመወሰንና በየወቅቱ ለማሻሻል የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የተመደቡ የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎች በሕገ- ወጥ መንገድ ይፋ እንዳይሆኑ፣ እንዳይጠፉ፣ እንዳይበላሹ፣ እንዳይለወጡ እና እንዳይተላለፉ ተገቢውን ጥበቃ ማድረግ በማስፈለጉ፤

በሀገሪቱ የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመመደብና ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል ግልፅ፣ ወጥ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 804/2005 አንቀጽ 28(1) እና በመገናኛ ብዙሃንና መረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2ሺ አንቀጽ 37(2) መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: ደንብ ቁጥር 539/2015
ቀን: ጳጉሜ 1፥ 2015 ዓ.ም.
Law Type: Regulations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

No data was found