ስለ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማ በህገ መንግሥቱ አንቀፅ 3 ንዑስ አንቀፅ (1) እና (2) የተደነገገ በመሆኑ፤
ይህንን ህገ መንግሥታዊ ድንጋጌ ተከትለው ቀደም ሲል የወጡትና በስራ ላይ ያሉት ህጐች ሰንደቅ ዓላማን በሚመለከት ያልሸፈንዋቸው እና ያልተመለከትዋቸው ጉዳዮች በመኖራቸው፤
ለሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌ አፈፃፀም ሰንደቅ አላማንና አርማን የሚመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮችን የሚወስን እና ቀደም ሲል የነበሩትን የተለያዩ ህጐች በአንድ ላይ የሚያጠቃልል አንድ ራሱን የቻለ ሕግ ማውጣቱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።