ከቦሌ የቀለበት መንገድ መተላለፊያ እስከ መስቀል አደባባይ ላለው የመንገድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚ ውል 411ሚሊዮን የቻይና ዩዋን (አራት መቶ አሥራ አንድ ሚሊዮን የቻይና ዩዋን) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በቻይና የኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል እ.ኤ.አ. ማርች 9 ቀን 2011 የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (02) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡