የዱር እንስሳት ሀብት ባልተቀናጀና አለአግባብ በሆነ አጠቃቀም ምክንያት እየተመናመነ በመምጣቱና ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁ፤
እስከዛሬ ለዱር እንስሳት እየተደረገ ያለው ጥበቃና እንክብካቤ ውጤታማ ሆኖ ባለመገኘቱ፤
በጥበቃ ቦታዎች አካባቢ የሚኖረውን ሕብረተሰብና የግል ባለሃብቶችን በዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረገ ጠቀሜታው የጎላ ስለሆነ፤
ቀደም ብለው የወጡትና እስከዛሬ የሚሠራባቸው አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች የጊዜውን ተጨባጭ ሁኔታ ያላገናዘበና አሁን ያለውን ፌዴራላዊ ሥርዓት የተከተለ ባለመሆናቸው፤
ከዱር እንስሳት ሀብት የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጥቅም በማጎልበት ለድህነት ቅነሳው ስትራቴጂ የሚኖረውን ሚና ማሳደግ የተገባ በመሆኑ፤
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•