በአገልግሎት ላይ

የኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ

ተመሳሳይ ፍላጎት ባላቸው ሰዎች መካከል በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ኅብረት በመፍጠር ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ንብረትንና ጉልበትን በማስተባበር የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የባህላዊና ሌሎች የጋራ ፍላጎቶችን በማሟላት እርስ በርስ መደጋገፍንና ቁጠባን የሚፈጥሩ የኅብረት ሥራ ማህበራትን ማቋቋም እና መምራት አስፈላጊ በመሆኑ፤

የኅብረት ሥራ ማህበራት በገጠር እና በከተማ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ በአባላት ምርት ላይ ዕሴት በመጨመር፣ የግብይት እና የፋይናንስ ትስስር በመፍጠር፣ አላስፈላጊ የገበያ ሰንሰለትን በማሳጠር፣ በሃገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በመሆን ለዜጎች የሥራ ዕድልን በመፍጠር በሀገሪቷ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ውስጥ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት በአንድ ወጥ ሃገራዊ የኅብረት ሥራ ማህበር አዋጅ በመመራት በሕገ መንግስታችን አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር የተቀመጠውን ዓላማ ለማሳካት ምቹ ሁኔታን መፍጠር በማስፈለጉ፤

የኅብረት ሥራ ማህበራት የሚከተሏቸውን መሠረታዊ መርሆዎችና ልዩ ባህሪ እንደጠበቁ በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ በማስፈለጉ፤

የአባላትን ባለቤትነት እና ተጠቃሚነት መብት የሚያረጋግጡ፣ አባላት የሚመሯቸውና የሚቆጣጠሯቸው ኅብረት ሥራ ማህበራትን ማደራጀት እና ማጠናከር በማስፈለጉ፤

የኅብረት ሥራ ማህበራትን ዓላማ ለማሳካት የኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁበትንና የሚመሩበትን ሕግ በማውጣት በሥራ ላይ ያለውን የኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ ፶፭ (፮) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፦

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 985/2009
ቀን: ታህሳስ 14፥ 2009 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations
Sector: Cooperatives

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 274/1994

ግንቦት 6፥ 1994 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ