በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በፖላንድ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል በገቢ ላይ የሚከፈለውን ግብር በሚመለከት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈፀምን ማጭበርበር ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ሐምሌ 6 ቀን 2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንን ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ሰኔ 22 ቀን 2009ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡