በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኮሪያ ሪፐብሊክ መንግሥታት መካከል በገቢ ላይ የሚከፈለውን ግብር በሚመለከት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈፀምን ማጭበርበር ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ግንቦት 17 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንን ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ 55 (1)እና(12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡