የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተዋንያን ዘርፉን በተቀናጀ መንገድ የሚመራበትን እና ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራር የሚሰፍንበትን ራዕይና አቅጣጫ በመተለም ውጤታማ የሆነ የኮንስትራክሽን ኢንዱሰትሪ ልማት በማሳደግ ረገድ ጉልህ እና የማይተካ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ፤
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለአገሪቱ አጠቃላይ ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የሚያግዙ የፖሊሲ ሀሳቦችን እና በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉት ክፍተቶች በጥናት እየተለዩ የመፍትሔ ሀሳብ የሚመነጭበት፣ አዋጭ የሆኑ ዓለም አቀፍ ልምዶች የሚቀመሩበትና ተግባራዊ የሚደረጉበትን ሥርዓት በተመለከተ የሚዘጋጁ ሕጎችና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ዘርፉን የበለጠ የሚያበለፅጉ እንዲሆኑ በማስፈን ኢንዱስትሪውን ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞች፣ሕጎችና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ዘርፉን የበለጠ የሚያበለፅጉ እንዲሆኑ ከማድረግ አኳያ ሀሳቦችን የሚያመነጭ እና የሚመክር አገራዊ ባለድርሻ መድረክ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው እና አግባብነት ባላቸው የምህንድስና፣ የአርኪቴክቸር፣ የቴክኖሎጂ ከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት እና የቴክኒክና ሞያ ተቋማት መካከል ትስስር በማጠናከር በጥናትና ምርምር የበለፀገ የሰው
ሀብት በማፍራት እና የተፈጠረውን የሰው ኃይል ክህሎት በመገንባት የኢንዱስትሪውን ፍላጎት እንዲያሟላ
በማድረግ የላቀ ብቃት እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያለው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መፍጠር እንዲቻል
ጉልህ ድርሻ የሚጫወት ምክር ቤት ማቋቋም በማስፈለጉ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮዽያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ 5 መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡
•