በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ በጥሬውና እሴት የተጨመረበት የቡና ምርት በጥራትና በከፍተኛ መጠን፣ ቀጣይነት ባለውና የምርት ዱካውን በጠበቀ ሁኔታ ለማቅረብ የሚያስችል የቡና ግብይትና ጥራት ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣
የቡና ግብይትን ዘመናዊነት፣ ህጋዊነትና ፍትሃዊነት በማሻሻል የቡና አምራቾች፣ የግብይት ተዋንያንና የሀገሪቱን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ማሳደግ የሚያስችል የተለያየ አማራጭ ያለው የግብይት ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግሥት አንቀፅ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•