በመንግሥት የምርምር ተቋማት የሚለቀቁ የዕፅዋት ዝርያዎች የመነሻ ዘር ተደራሽነትን በማሳደግ አርሶ/አርብቶ አደሩ አዳዲስ ከሚለቀቁ ዝርያዎች የሚገኘውን ትሩፋት ፈጥኖ ተጣቃሚ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፤
በመንግሥት የምርምር ተቋማት የተለቀቁ የዕፅዋት ዝርያዎችን አንዱ ድርጅት ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ ሲያስተዋዉቅ ሌላው ያለ ወጪ የዘር ገበያው ላይ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ በመኖሩና ይህም በዘር አባዦች በኩል ያለውን የዝርያየማስተዋወቅ ስራን ያዳከመ መሆኑ በግልጽ በመታየቱ፤
የግልና የመንግሥት አጋርነት በማጠናከር በዘር ስርዓቱ ውስጥ ያለውን የመነሻ ዘር አቅርቦት ችግር መቅረፍ የሚቻል በመሆኑና በመንግሥት የምርምር ተቋማት የሚለቀቁ የዕፅዋት ዝርያዎች ላይ ጤናማ ውድድርን ማስፈን በማስፈለጉ፤
የግብርና ሚኒስቴር በዕጽዋት አዳቃዮች መብት አዋጅ ቁጥር 1068/2010 አንቀጽ 32/2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡