በእንስሳት መድኃኒት ምርት ላይ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶችን በመቆጣጠር የእንስሳት ጤና እና ደኅንነትን እንዲሁም የህብረተሰቡን ጤና መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ፤ ደህንነቱ፣ ጥራቱ እና ፈዋሽነቱ የተጠበቀ የእንስሳት መድኃኒት ለማምረት የአከባቢ እና የግንባታሁኔታ፣ የመሣሪያዎች አተካከል፣የማገልገያ መስመሮች አዘረጋግ ፣ የሠራተኛ ሁኔታ በተጨማሪም ቅድመና የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን አስፋላጊ በመሆኑ፤
በሀገሪቱ የሚረቱ የእንስሳት መድኃኒቶች ጥራታቸውን የጠበቁና የመልካም አመራረት አተገባበር መርሆችን ተከትለው እንዲመረቱ ማድረግ አስፈላጊ በሆኑ ፤ ማንኛወም የእንስሳት መድኃኒት አምራች የዚህን መመሪያ ድንጋጌዎች እና ሌሎች ተፈጻሚ ሕግጋትን ጥሶ ሲገኝ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ እንዲሰረዝ ፣ እንዲታገድ ወይም ሌሎች አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ ተገቢ በሆኑ፤ የ
ሀገሪቱን የእንስሳት መድኃኒት በመጠን ፣ በጥራት እና በስብጥር ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤ ደንብ እና የተለያዩ መሠረታዊ መርሆችን በተመለከተ ልዩነት የሚንጸባረቅባቸውን ብሔራዊ ሕግጋት፣ አስተዳደራዊ ድንጋጌዎች አንድ ላይ በማጣጣም በእንስሳት ጤና እና በህብረተሰብ ጤና ብሎም በአካባቢ ደኅንነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሳያሳድር በሀገር ወስጥ የእንስሳት መድኃኒት አምራች ድርጅቶች እንዲበረታቱ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 728/2004 አንቀጽ 28(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡