የመመሪያ መለያ: 746/2013
ቀን: የካቲት 12፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

በ7ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የከተሞች ራስን የማስተዋወቅ ውድድር ማስፈጸሚ መመሪያ ቁጥር 746/2013

በኢትዮጵያ ፈጣን የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የከተማ ነዋሪዎችንና የሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማጠናከር መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት የከተማ ልማት ፖሊሲ እንዲሁም ፖሊሲውን መነሻ ተደርገው የተዘጋጁ ስትራቴጂዎች እና ኘሮግራሞች ትግበራና ስኬት ማፋጠን ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በተለያዩ ከተሞች አስተናጋጅነት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር በመሆኑ፣

የኢትዮጵያ ከተሞች በአሁኑ ወቅት በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ከፍተኛ እድገት እያስመዘገቡ እና ለአገራዊ ምጣኔ ሃብት ዕድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እያደገ የመጣ ስለሆነ ከተሞች የልማት ሥራዎቻቸውን የሚያሳዩበት፣ እርስ በእርስ የሚማማሩበት፣ ለነዋሪዎቻቸው እና ለባለድርሻ አካላት አስፈላጊ መረጃ የሚሰጡበት፣ እንዲሁም የኢንቨስትመንት፣ የቱሪዝም፣ የገበያና የሌሎች መስህቦቻቸውን የሚያስተዋውቁበት የከተሞች እራሳቸውን የማስተዋወቅ ሥራ (City Marketing) ማካሄድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በአገር-አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በማካሄድ ከተሞችን እርስ በእርስ በማወዳደር ዕውቅና እና ሽልማት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የከተሞች እራሳቸውን የማስተዋወቅ ውድድሩን ግልጽ፣ ፍትሃዊ እና በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል መስፈርት በማዘጋጀት መምራት የሚገባ በመሆኑ ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ሚያዝያ 8÷2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
Addis Ababa City Administration Labor and Social Affairs Bureau
ሚያዝያ 8÷2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
Addis Ababa City Administration Labor and Social Affairs Bureau
ሚያዝያ 8÷2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
Addis Ababa City Administration Labor and Social Affairs Bureau