በከተማችን ውስጥ የሚገኙ ስራ ፈላጊ ነዋሪዎችን በመለየት አስፈላጊውን ሥልጠና ማመቻቸት፤ ማደራጀት፤ የፋይናንስ አቅርቦት፤ የመስሪያ ቦታ እና የገበያ ትስስር ድጋፎች እንዲያገኙ በማድረግ ሰፊ የስራ ዕድል እንዲፈጠር እና በሃገራችን የሚታየውን ስራ አጥነትና ድህነት መቀነስ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂን መሠረት በማድረግ ኢንተርፕራይዞች እንደ የዕድገት ደረጃቸው ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የድጋፍ ማዕቀፎች በማዘጋጀት በማስፈለጉ፤
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ አወሳሰንና ሽግግር አፈጻጻም መመሪያ የተስተዋሉ ያልተመለሱና ያልተፈቱ ችግሮች ለመፍታትና ኢንተርፕራይዞችን ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል እንዲያገኙ ለማድረግ እና ግልጽነትና ተጠያቂነት ሥርዓት በማካተት ሥራውን መምራት በማስፈለጉ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ተግባርና ኃላፊነታቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡