የማሻሻያው አስፈላጊነት የመደኅንነት፣ ጤንነትና የሥራ አካባቢ አገልግሎት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሰብዓዊ ገጽታ ያለው ሲሆን በሥራ ላይ ለተሰማራው አምራች ኃይል ምቹ የሥራ አካባቢ በመፍጠር፣ ንብረትን ከድንገተኛ አደጋ በማጠበቅ፤ ምርታማነትን በማሳደግ፤ የሥራ ቅልጥፍናና ጥራትን በማሳደግ በግብዓዊ ወስጥ ተወዳዳሪና ተሸላሚ እንዲሆን በማስቻል ሠራተኛውን ከኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና አካላዊ ጉዳት ይከላከላል፤ ደህንነቱንና ጤንነቱን ያረጋግጣል።
በሥራ ቦታዎችና አካባቢዎች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ፣ ደህንነቱና ጤንነቱ የተጠበቀ ምርታማና ወታማ አምራች ኃይል ለመፍጠር ከሚያስችሉ እርምጃዎች መካከል በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም አንቀጽ 92/2 በተቀመጠው መሠረት በድርጅቶችና ኢንዱስትሪዎች የአደጋ ተከላካይ ሠራተኛ (Safety Officer) መደብ እና የመደኅንነትና ጤንነት ተከታታይ ኮሚቴ ማቋቋም ወሳኝ ነው።
ይህም የሥራ ቦታዎችና አካባቢዎች በሠራተኞች ደኅንነትና ጤንነት ላይ አደጋ የማያስከትሉ እና ምቹ (Decent Work) መሆናቸውን ለማረጋገጥ ያስችላል። በመሆኑም 377/96 ዓ.ም ተሻሽሎ በአዲሱ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም መሠረት ከመስከረም 1998 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረው “የመደኅንነትና ጤንነት ተከታታይ ኮሚቴ አቋቋም” የወጣ መመሪያ በለስና አስፈላጊ ማሻሻያ በማድረግ ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ ተደርጓል።