በኢትዮጵያ ፈጣን የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የከተማ ነዋሪዎችንና የሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማጠናከር መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት የከተማ ልማት ፖሊሲ እንዲሁም ፖሊሲውን መነሻ ተደርገው የተዘጋጁ ስትራቴጂዎች እና ኘሮግራሞች ትግበራና ስኬት ማፋጠን ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በተለያዩ ከተሞች አስተናጋጅነት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር በመሆኑ፣
የኢትዮጵያ ከተሞች በአሁኑ ወቅት በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ከፍተኛ እድገት እያስመዘገቡ እና ለአገራዊ ምጣኔ ሃብት ዕድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እያደገ የመጣ ስለሆነ ከተሞች የልማት ሥራዎቻቸውን የሚያሳዩበት፣ እርስ በእርስ የሚማማሩበት፣ ለነዋሪዎቻቸው እና ለባለድርሻ አካላት አስፈላጊ መረጃ የሚሰጡበት፣ እንዲሁም የኢንቨስትመንት፣ የቱሪዝም፣ የገበያና የሌሎች መስህቦቻቸውን የሚያስተዋውቁበት የከተሞች እራሳቸውን የማስተዋወቅ ሥራ (City Marketing) ማካሄድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በአገር-አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በማካሄድ ከተሞችን እርስ በእርስ በማወዳደር ዕውቅና እና ሽልማት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የከተሞች እራሳቸውን የማስተዋወቅ ውድድሩን ግልጽ፣ ፍትሃዊ እና በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል መስፈርት በማዘጋጀት መምራት የሚገባ በመሆኑ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 916 2008 አንቀጽ 26 የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት በአግባቡ ለመተግበር ይችል ዘንድ ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡