❖ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያወጣውን የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 6/2000 እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰራተኞች የዲሲፕሊን አፈፃጸምና ቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ቁጥር 24/2002ን መሠረት ያደረገ የዲስፕሊን አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት በማስፈለጉ፣
❖ የዲሲፕሊን አፈፃፀም አልፎ አልፎ ከመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር አዋጅና ደንብ ውጭ ወጥነት ሳይኖረው ሲፈፀምና የዲስፕሊን እርምጃዎች ሥልጣኑ በሌላቸውና ተገቢውን ሥነ-ሥርዓት ባልተከተለ መልኩ እ ተ ናሙ በመሆናቸው ሥርዓት ማስያዝ ተገቢ በመሆኑ፣
❖ መልካም አስተዳደርን የማስፈን ጥረት አግባብ ባላቸው ህጐች፣ መመሪያዎችና አሠራሮች ማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
❖ ሠራተኛው በዲስፕሊን አፈፃፀም ጉድለት ሲከሰስ ሊከተል ወጁም ሊ ም የሚገባውን ሥነ-ሥርዓት ባለማወቅ በራሱም ሆነ በመስሪያ ቤቱ በአፈጻጸም ላይ ችግር እንዳይከስትና ለተቀላጠፈና ወጥነት ላለው አሠራር የሚያግዝ በመሆኑ፣
እነዚህንና የመሳሰሉትን የአፈጻጸም ችግሮች ለመፍታት እንዲረዳ በመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 6/2002 አንቀጽ 94(2) እና በደንብ ቁጥር 24/2002 አንቀጽ 53 መሠረት ይህ የአፈጻጸም መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ ወጥቷል::