የሰው ሀብት ብቃትና አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ በሀብት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ስር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን፣ በሚኒስቴር መ/ቤቱ በአስተዳደር ዘርፍ የሚገኙ የሰው ሀብት የማስተዳደር፣ የማደራጀት እና የአቅም መገንባት ስራዎችን የሚያከናውን ነው። የሥራ ክፍሉ በሲቪል ሰርቪስ የሰራተኞች አስተዳደር በተቀመጡ ሕጎች ማለትም አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ እና የአሠራር ሥርዓት መሠረት በማድረግ የሰራተኞች የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊንና የቅሬታ ማስተናገጃና ሥራዎችን ያከናውናል። በተጨማሪ በተቋሙ ውስጥ ምቹ የሥራ አካባቢ እንዲፈጠር በማድረግ የሰራተኞችን የሥራ ተነሳሽነት እንዲጎለብት ይሰራል። ከሰው ሀብት አስተዳዳር ጋር የተያያዙ ዘመናዊ የአሠራር ማሻሻያ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለሰራተኞች የመስጠት፣ ለተቋሙ ሰራተኞች ለሥራ የሚስፈልጉ ጥቅማ ጥቅምና የሚያገኙበትንና እንዲሁም ለአቅም ማጎልበቻ የሚሆኑ ሥልጠናዎች ሰራተኞች እንዲያገኙ ይሰራል። ሰራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ሊያስገኙ የሚችሉ መረጃዎች፣ የሥራ አፈጻጸም ውጤት እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የግል ማህደር በማደራጀት መያዙን የማረጋገጥ ሥራ ያከናውናል።
