በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን የመከላከልና መቆጣጠር ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ የተዘጋጀ የግብዐት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሄደ

Stakeholder Input Gathering Forum Held on the Draft Amendment Proclamation for the Prevention and Control of Money Laundering and Terrorism Financing

በመድረኩ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ በሀገራችን ያለው የፋይናንስ ስርዐት ደህንነቱ የተጠበቀ እና አለማቀፋዊ ግዴታዎችን በሚያሟላ መልኩ በተቀረፀ ስርዐት መመራት የሚኖርበት በመሆኑ የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት አብራርተው ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልእክት ካስተላለፉ በኋላ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዩን ጢሞቲዮስ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩም የመድረኩን ተሳታፊዎች አመስግነው በሚቀረበው ሰነድ ላይ በንቃት በመሳተፍ ለረቂቁ መዳበር አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ በንግግራቸው አስታውሰዋል፡፡

በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣን አዋጅ ለማሻሻል አለማቀፍ መለኪያዎችን እና ግዴታዎችን ማሟላት የሚገባው በመሆኑ እና ከዚህ በፊት በአዋጁ ትግበራ እና አተረጓጎም ግዜ የገጠሙ ችግሮችን በመቅረፍ ድንጋጌዎችን ግልፅ እና ለትርጉም በማያሻማ መልኩ መደንገግ በማስፈለጉ አዋጁን ለማሻሻል ምክንያቶች ሆነዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በተለያየ የመሠረታዊ እና ሥነ-ሥርዐታዊ ህጎች ተበታትነው ሲሰሩባቸው የነበሩ የሀብት ማስመለስ ህጎችን አንድ ወጥ ወደሆነ ስርዐት መሰብሰብ በማሰፈለጉ እና ለአሰራረም የሕግ ክፍተት የነበረባቸውን ጉዳዮች በሕግ መምራት በማስፈለጉ የንብረት ማስመለስ እና ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ይዞ መገኘትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ረቂቅ ህጎችም ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ባለድርሻ የመንግሥት ተቋማት፣ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የሕግ ምሁራን እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

Tagged Under: amendment anti-money anti-money laundering asset Asset Recovery Civil Society Organizations compliance counter-terrorism counter-terrorism financing draft ethiopian federal democratic republic (fdre) financial Financial Crimes Financial Institutions financial security financing illicit financial flows International Standards laundering legal framework money Money Laundering recovery Security Stakeholder Consultation terrorism Terrorism Financing
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች