በድሬዳዋ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች የንቃተ ህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

Legal Awareness Training Provided to Community Representatives from Various Sections of Society in Dire Dawa City

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ዳሬክቶሬት ወንጀልን በመከላከል የህብረተሰቡ ሚና እና በሀሰተኛ ሰነድ ዝግጅትና መጠቀም ወንጀል ዙሪያ ከህዳር 19-20/2016 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

የሥልጠናውም ዋና ዓላማ የፍትሕ ተቋማት ያለ ህብረተሰቡ ዕገዛ፣ ተሳትፎ እና ድጋፍ ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን እንደማይችሉ እና ማህበረሰቡ በየግዜው ከሚወጡ አዳዲስ የወንጀል መከላከል ህጎችና አሰራሮችን እንዲላመዱ ለማድረግ እና ውስብስብ የወንጀል ተግባሮች ስለሚፈጸሙበት መንገድ ፣ ስለ ወንጀል መከላከል፣ ጥቆማ አሰጣጥና አቀራረብ እንዲሁም የተቀመጡ ልዩ ልዩ የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች ምን እንደሆኑ ሰፊ ግዛቤ ማስጨበጥ መሆኑን አቶ አያልቅበት ግሩም በፍትሕ ሚኒስቴር ንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከፍትሕ አጋዥ አካላት ተሳትፎ ውጪ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ሆነ ፍትሕን ማስፈን ስለማይቻል የህበረተሰቡን ተሳትፎና ትብበር ለማጠናከር ተቋሙ የንቃተ ሕግ ትምህርትን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና እንዳለው ተብራርቷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት እና መገልገል ዙሪያ የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነትን በተመለከተ ደግሞ ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በመገልገል ወንጀልን በመከላከል ረገድ ህብረተሰቡ ጉልህ ሚና እንዳለው በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በተያያዘም በጉዳዩ ላይ ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ ማህበረሰቡ ለፍትሕ አካላት ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ወንጀለኞችን ለሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማስቻል ፣ ተገቢውን የፍትሕ እገዛ በማድረግ መብቱንም እንዲጠይቅ ለማድረግ እና የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በማስቻል ረገድ ተገቢ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በጨረሻም በዚህ ሥልጠና በሁለት ዙር ከ200 በላይ ሰልጣኞች የተሳተፉ ሲሆን ወደፊት በሌሎች የሥልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለከተማው ነዋሪዎች እና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተከታታይ የሆነ ሥልጠና ሊሰጥ እንደሚገባ የሥልጠናው ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

Tagged Under: Awareness • Capacity Building • civic engagement • community • community participation • Crime • Crime Prevention • criminal law • dawa • democratic • dire • Dire Dawa • FDRE • federal • federal democratic republic of ethiopia (fdre) • forged • forged documents • Fraud Prevention • Justice System • legal • Legal Accountability • legal awareness training • Legal Education • participation • prevention • public awareness campaign • republic • Rule of Law • Training • witness testimony
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች