የአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ ፍትህ ማዕከል በይፋ ተመርቆ አገልግሎት ጀመረ

Induction Training Being Given to Newly Employed Prosecutors at the Dire Dawa Branch Office of the Federal Democratic Republic of Ethiopia Ministry of Justice

ይህ የአዲስ አበባ ከተማ የማኅበረሰብ ፍትሕ ማዕከል በሙከራ ትግበራ ደረጃ ተመርጦ ስራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን የተመረቀው ማዕከልም የባህላዊ ሽምግልና ስርዓቱን ለማካሄጃ የሚያገለግል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ በመገኘት ለእንግዶች የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ሲሆኑ፤ በዚህም የፍትሕ አገልግሎቱ በመንግሥት ስር ብቻ የተወሰነ በመሆኑ የህብረተሰቡን ባህላዊ የሽምግልና ስርዓቶች ሳያስተናግድ ለአመታት መቆየቱን አስታውሰው፤ ይህ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተጀመረው የሙከራ ፕሮግራም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ህብረተሰቡ የሚገለገልበትን ተጨማሪ አማራጭ የፈጠረ ከመሆኑም ባሻገር ዘላቂነት ያለው እድገት እና መልካም አስተዳደር ለማስገኘት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በማኅበረሰብ ፍትሕ ማዕከል የምረቃ ስነስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሀን በበጉላቸው በ2010 በሀገሪቱ የነበረውን ለውጥ ተከትሎ የሪፎርም ስራዎች ከተሰራባቸው ዘርፎች መካከል አንዱ ፍትሕ ሴክተር እንደነበር አስታውሰው፤ በዚህም በፍትሕ ላይ የነበሩ ችግርች ምንድናቸው በሚል ጥናት ተደርጎ አፋኝ ወይም ጨቋኝ የሆኑ ህጎች አሉ በሚል ተለይቶ ለአብነት በሲቪል ማኅበረሰብ፤ በሽብር ሕግ እና ሌሎች ህጎች ላይ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን፤ በሌላም በኩል ነፃ አይደሉም የተባሉ የፍትሕ ተቋማት ላይ የማሻሻያ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ በ2014ዓ.ም ደግሞ አጠቃላይ ያሻሻልናቸው ህጎችና ተቋማት ለውጥ ማምጣት ችለዋል ወይ በሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የዳሰሳ ጥናት በማድረግ በዘርፉ ውስጥ የመጡ አዎንታዊ ለውጦች እንዳሉ ሆነው፤ በከተማ ሆነ በገጠር አካባቢ የሚገኘው ማህበረሰባችን በእለት ከዕለት የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለምሳሌ ከመሬት፣ ከቤተሰብ ውስጥ ግጭት፣ ከውርስ፣ ከብድር እና ሌሎች ጉዳዮች አንፃር በምስክርና ተከሳሽ አለመቅረብ ወዘተ ምክንያቶች በዓመት ውስጥ በፍርድ ቤቶች በኩል መፍትሄ እያገኙ ባለመሆኑ አብዛኛው ሰው ባህላዊ የሽምግልና ዘዴዎችን ወደ መጠቀም እየሄደ መሆኑን በጥናት ማወቅ መቻሉን ተናግረው፡፡

በዚህ ጥናት መነሻነት መገንዘብ እንደተቻለው በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ባህላዊ የሽምግልና ስርዓቶች በመደበኛ የሕግ መንገድ ሊሸፈኑ ያልቻሉ ጉዳዮችን እየተመለከቱ በጥሩ ሁኔታ መፍትሄ እየሰጡ መሆናቸው በመታወቁ፤ እነዚህን ባህላዊ ስርዓቶች በመደገፍ እጅግ በርካታ ጉዳዮችን እንዲፈቱ በማድረግ ለፍትሕ ስርዓቱ አዎንታዊ የሆነ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማድረግ መቻሉን ተናግረው፤ በዚህም በህብረተሰቡ መካከል ሰላም እንዲፈጠር ከማድረጉ ባሻገርም በዜጎች ላይ ለፍትሕ ፍለጋ ይወጣ የነበረውን ገንዘብ እና የሚባክነውን ጊዜ በማስቀረት ረገድ ዉጤቶች መታየታቸውን አስረድተው፤ በአዲስ አበባ ከተማ ይሄንን ስራ ለሚያከናውኑ አካላት ማረፊያና መስሪያ የሚሆን ቦታ ተዘጋጅቶ እንዲከፈት መደረጉ መልካም ጅምር መሆኑ እና በቅርቡም በአፋር እና ሲዳማ ክልሎች ተመሳሳይ ማዕከላት ተከፍተው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ገልፀው፤ በአጠቃላይ ይህ ስራ ለረጅም ዘመናት ሳንጠቀምባቸው የቆዩ ባህላዊ እሴቶቻችንን በመጠቀም የህብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ችግሮች ተከታትሎ ለመፍታት የሚያግዙ ውጤት የተገኘበት በመሆኑ ፍትሕ ሚኒስቴር ለወደፊትም ቢሆን ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከጥናት ጀምሮ የማኅበረሰብ ፍትሕ ማዕከላቱን በማቋቋም ረገድ ሰፊ ድርሻ እያበረከ የሚገኘው ‘ሂል’ የተሰኘው ግብረሰናይ ተቋም ስራ አስካሀጅ የሆኑት ሚስተር ሳም ሙለር በምርቃ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ከምንም ነገር በላይ ትላንትና፣ ዛሬን እና ነገን በህብረት የሚል አቋም ይዞ መሥራት ጠቃሚ መሆኑን ጠቅሰው የሕግ ባለሙያው እንዳለ ሆኖ ህብረተሰቡን ባህላዊ እውቀት አንድ ላይ እድርጎ መጠቀም ጠቀሜታው ሰፊ መሆኑን በመናገር፤ ተቋማቸው ፍትሕ ለሰው ልጆች በሙሉ መዳረስ አለበት የሚል እምነት እንዳለውና እሱን መነሻ በማድረግ የፍትሕ ስርዓቱን ቀላል፤ ተደራሽ፣ በአነስተኛ ወጪ ሊገኝ የሚችል፣ እና ውጤታማ ለማድረግ በአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት ውስጥ ፍትሕን ለህብረተሰቡ በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸውን አስታውሰው፤ ተቋሙ በኢትዮጵያ ውስጥ ተመሳሳይ የሆኑ ማዕከላትን በማስፋፋት ረገድ የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ ማበርከቱን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የማኅበረሰብ ፍትሕ ማዕከል ውስጥ ለማገልገል ከተለያዩ የሲቪክ ማኅበረሰብ አደረጃጀቶች ውስጥ የተመረጡ 15 የሀገር ሽማግሎዎች ቀርበው ከተዋወቁ በኋላ፤ በሰጡት አስተያየት የተሰጣቸው አደራ ከፍተኛ በመሆኑ በመደበኛው የፍትሕ ስርዓት ሊሸፈኑ ያልቻሉ ጉዳዮችን በባህላዊ ሽምግልና ስርዓት እየተመለከቱ በመዳኘት በታማኝነትና በሀቀኝነት ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም የማኅበረሰብ ፍትሕ ማዕከሉን በማደራጀት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለቸዋል፡፡

Tagged Under: Dire Dawa Legal ethics Legal induction Prosecutor training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች