የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው አሸናፊ ጌታቸው የተባለው ተከሳሽ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝግቦ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በሚገኘው የንግድ ቤት ቁጥር ውስጥ በንግድ ስራ ተሰማርቶ ሲሰራ ጥር 29 ቀን 2013 ዓ.ም ምንም አይነት ሽያጭ ሳያከናውን ከሚጠቀምበት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ 3 ሚሊዮን 720 ሺ 204 ብር የግብይት ዋጋ የያዙ 5 የደረሰኝ ቁጥሮች ለቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስለቆረጠ በፈፀመው ግብይት ሳይፈፅም ደረሰኝ መስጠት ወንጀል በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዐቃቤ ሕግ በፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120(4 እና 5) መሠረት ክስ መስርቶበት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የጉሙሩክና ታክስ ወንጀል ችሎት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ 4 ዓመት ከ6 ወር ተቀጥቶ የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ ቅጣቱ አንሷል በማለት ይግባኝ ጠይቆ ተከሳሹ በ5 ዓመት ከ6 ወር እስራትና በ250 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡