ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሲካሄድ የቆየው አራተኛው ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ (ዩ.ፒ.አር) የስብአዊ መብቶች ረቂቅ አገራዊ ሪፓርት ውይይት ተጠናቀቀ

Fourth Universal Periodic Review (UPR) Draft National Human Rights Report Consultation with Various Stakeholders Concludes

4ኛ ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ የስብአዊ መብቶች ረቂቅ አገራዊ ሪፓርት የግብዓት ማሰባሰቢ የውይይት የመጨረሻ መድረክ የዩ.ኤን ውመን ፣የሲቪክ ማኅበረሰብ እና የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እና ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምስክር ታሪኩ በመድረክ መክፈቻ ንግግራቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ከምታደርግባቸው ስምምነቶች አንፃር ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ የሰብዓዊ መብት ግምገማ አንዱ መሆኑን አንስተው የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ ላይ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እየተሰጡ ያሉ ግብዓቶችን በተገቢው ቦታ በማካተት ሪፖርቱ የተደራጀ ፣ታዓማኒ ፣ሁሉን አቀፍ እና ሀገራችንን የሚገልፅ እንዲሆን ለማስቻል የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ምክረ ሀሳብ ሪፖርቱን ሙሉ እንደሚደርገው ተናግረዋል፡፡

በሕግ ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ትብብር ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የሱፍ ጀማው ሀገራችን 4ኛውን ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ የሰብዓዊ መብቶች ግምገማ ሪፖርት ግምገማን አስመልክተው ለመድረኩ ተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል፤የቀረበውን ገለፃ ተከትሎ ተሳታፊዎች የሪፖርት ሰነዱን አስመልክቶ ያላቸውን ምክረ ሀሳብ በቡድን እንዲመክሩ በማድረግና በቡድን ውይይቱ ወቅት የታዩትን ክፍተቶች፣ መጨመር አለባቸው ፣ ቢብራሩ ፣ቢወጡ ፣ቢጠቀሱ እና ቢስተካከሉ ያሏቸውን ሀሳቦች በግልፅ አስቀምጠዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ የሱፍ በቡድን የተሰጡ ምክረ ሀሳቦችን ተቀብለው በሪፖርቱ እንደሚያካትቱ ጠቅሰው በቀጣይ የሚሰጡት ምክረ ሀሳብ ካለ መቀበል እንደሚቻል አሳውቀው ተሳታፊዎች ላደረጉት አስተዋፅኦ በማመስገን የእለቱ መድረክ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: amharic civil civil liberties Civil Society Consultation draft report feedback fundamental rights Government human Human Rights human rights monitoring human rights report Justice Justice Ministry national human rights institution national report periodic recommendations report review Rights society stakeholder Stakeholder Consultation un universal Universal Periodic Review UPR
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች