በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ተጠናቆ ለህትመት በቃ!!

Ethiopia's First Encyclopedic Law Dictionary Completed and Published!!

የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ እና ከጄስቲስ ፎር ኦል ፒ.ኤፍ. ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ምረቃ ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ሰዓት የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችና የፍትሕ ዘርፉ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞትዮስ ከሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በእለቱ ተገኝተው ይሕንን በሀገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነዉን የሕግ መዝገበ ቃላትን በይፋ መርቀዋል።

Tagged Under: Legal Terminology
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች