በሀገር ደረጃ ከመሬት ጋር ተያይዞ ለሚፈጠሩ ግጭቶች አፈታት ዙሪያ የሕግ ባለሙያዎች ሊጠቀሙበት የሚያስችል ጋይድ ላይን ዝግጅት ግብዓት እንዲሆን ታስቦ የቀረበውን ጥናት ገምግሞ ግብዓቶችን ለመለየትና ለማሻሻል የሚያስችል ውይይት መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም በፍትሕ ሚኒስቴር አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
የውይይት መድረኩን ፍትሕ ሚኒስቴር ከHIIL Institute እና Desty Ethiopia ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ከተለያዩ የሕግ ምሁራን የተውጣጣ የባለሙያዎች ኮሚቴ የተሳተፉበት መሆኑን በፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሕ ስርዓት ማሻሻያ እና የለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኖህ ታከለ ገልፀዋል፡፡
በመሬት ግጭት አፈታት ዙሪያ ለሚዘጋጀው ጋይድ ላይን ግብዓት የተደረገው ጥናት በገለልተኛ አማካሪ የተጠና መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የባለሙያዎች ኮሚቴው በጥናቱና ምክረ ሃሳቦች ላይ በዝርዝር በመወያየት ግብዓቶችን በመለየት የማሻሻያ ሃሳቦችን ሰጥተዋል፡፡
ይህ ውይይት ለ2ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን አቶ ኖህ የጠቆሙ ሲሆን በዚህ ውይይት የተለዩ ግብዓቶች እና የማሻሻያ ሃሳቦች ተካተውበት 3ኛ እና የመጨረሻ ዙር ውይይት እንደሚካሄድ ገልፀዋል፡፡