የተለያዩ ማታለያዎችን በመጠቀም ወደ ግል ተበዳዮች ስልክ በመደወል የሚነገራቸውን ቁጥር በመንካት ገንዘብ እንዲያስተላልፉለት በማድረግ ከ300 ሺ ብር በላይ የወሰደው ተከሳሽ በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ

Defendant Sentenced to Rigorous Imprisonment and Fine for Defrauding Over 300,000 Birr by Using Various Deceptions and Tricking Victims into Transferring Money Over the Phone

በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ላይ ሜጋ ማንዴላ ማለቆ የተባለው ተከሳሽ በተለያዩ 6 ክሶች የተከሰሰ ሲሆን፤ በክሱ ዝርዝርም ተከሳሽ የሌላን ሰው የተሳሳተ እምነት በመጠቀም ካልተያዙ ግብረ-አበሮቹ ጋር በመሆን ከህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ 6 ቀናት ለተለያዩ ግለሰቦች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ በመደወል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደደወሉ በማስመሰል የተለያዩ ማታለያዎችን በመጠቀም እነሱ የሚነግሯቸውን ቁጥር በስልካቸው እንዲነኩ በማድረግ በ1ኛ ክሱ ላይ 11ሺ 10 ብር፣ በ2ኛ ክሱ ላይ 64ሺ 900 ብር፣ በ3ኛ ክሱ ላይ 8ሺ 300 ብር፣ በ4ኛ ክሱ ላይ 199ሺ 400 ብር፣ በ5ኛ ክሱ ላይ 68ሺ ብር፣ በ6ኛ ክሱ ላይ 19ሺ 600 ብር ከተበዳዮች ሂሳብ ቁጥር ላይ ተቀናሽ ሆኖ ተከሳሽ ሀሰተኛ ስም እና መታወቂያ ተጠቅሞ ወደከፈተው ሂሳብ ቁጥር እንዲያስተላልፉ ያደረጉ ሲሆን ተከሳሽም የገባውን ብር ከአካውንቱ ላይ ያወጣው በመሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ በፈፀመው በኮምፒዩተር አማካኝነት የሚፈፀም የማታለል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክር የለኝም በማለቱና በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠትና የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ6 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

Tagged Under: computer • Computer Fraud • conviction • Criminal Code • cybercrime • defendant • Documents • embezzlement • Federal High Court • financial • Financial Fraud • fine • forged • forged documents • Fraud • identity • Identity Theft • illegal • illegal money transfer • impersonation • phone • Prosecutor General • Rigorous Imprisonment • sentence • Theft
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች