ሀገሪቱ ከ672 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ ያደረገው ተከሳሽ በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጣ

Defendant Sentenced to Prison and Fine for Causing Over $672,000 USD Foreign Currency Loss to the Country

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ከብሔራዊ ባንክ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው ሀገራችን ከ672 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ አድርገሀል ባለው ግለሰብ ላይ ክስ መስርቶበት በ6 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በ30 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ እንዲሁም የተከሳሽ ህዝባዊ መብቶቹ ለ2 ዓመት እንዲታገዱ ሲል ወስኖበታል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ከድር ሽሞሎ አሊ በተባለው ተከሳሽ ላይ ክስ ሊመሰርት የቻለው በ2000 ዓ.ም የወጣውን የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀጽ 3/1/ እና 58/1/ ስር የተደነገገውን ተላልፏል በሚል ነበር፡፡

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የባንክ ስራን ለመሥራት ከብሔራዊ ባንክ የተሰጠ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው ካልተያዙት ግብረ-አበሮቹ ጋር በመሆን ከቀን 03/05/2004 ዓ.ም እስከ ቀን 01/07/2008 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት በሳዑዲ አረቢያ እና ዱባይ ሀገር የሚገኙ ግለሰቦች ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ሲፈልጉ እዚያው ሀገር የሚገኙት ያልተያዙ ግብረ-አበሮቹ ገንዘቡን ተቀብለው በስልክ መልዕክት የሚላክላቸውን ሰዎች ስም፣ አድራሻ እና የገንዘቡን መጠን በሚያስተላልፉለት መሠረት ገንዘቡን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ አምስት ግለሰቦች እና እንዲሁም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀረበው ኦዲት ሪፖርት ውስጥ ለተጠቀሱት ግለሰቦች ለ1,643 ጊዜ በሐዋላ መልዕክት በጠቅላላው ብር 13 ሚሊዮን 182 ሺ 200 ብር የተለያዩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎችን በመጠቀም ወደ ተለያዩ የሐገሪቱ ክፍሎች በመላኩ ይኸውም በህጋዊ ገንዘብ አስተላላፊዎች አማካኝነት ገንዘቡ ቢላክ ኖሮ ሐገሪቱ ልታገኝ የነበረውን 672 ሺ 701 የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ ያደረገ በመሆኑ ያለፈቃድ የባንክ ስራ መሥራት ወንጀል ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበታል፡፡

ተከሳሹ የተከሰሰበት ክስ በችሎት ተነቦለት የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ብሎ ክዶ ተከራክሯል። ዐቃቤ ሕግም ተከሳሹ ክዶ የተከራከረ በመሆኑ ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል። ፍርድ ቤቱም የቀረቡለትን ማስረጃዎች መርምሮ ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ስር እንዲከላከል ብይን ከሰጠ በኋላ ተከሳሽ ያልቀረበ በመሆኑ በሌለበት ፍርድ በመስጠት ተከሳሹ ይከላከል በተባለበት ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ነህ ብሎታል፡፡

በስተመጨረሻም ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎትም ተከሳሽን ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ያስተምራል በሚል በ6 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በ30 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ እንዲሁም የተከሳሽ ህዝባዊ መብቶቹ ለ2 ዓመት እንዲታገዱ ሲል ወስኖበታል፡፡

Tagged Under: activities amharic law bank Bank Fraud Banking civil rights suspension Criminal Sentencing Cross-Border Crime currency dubai exchange Federal High Court Financial Crime fine foreign foreign currency exchange Fraud illegal illegal money transfer imprisonment laundering money Money Laundering National national bank of ethiopia saudi arabia transfer unauthorized
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች