የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በማንኛውም ሁኔታ ልዩነት ሳይደረግባቸው በቀጥታ እና በነፃነት በመረጧቸው ተወካዮች አማካኝነት ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ስልጣናቸውን በተግባር ላይ ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ፤
ማንኛውም የምርጫ እንቅስቃሴ ዓለምአቀፍ የምርጫ መርሆዎችን አካትቶ በያዘ ህግ እንዲመራ ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በየደረጃው በሚካሄዱ ሁሉአቀፍ በእኩልነት ላይ የተመሰረተና በሚስጢር ድምዕ አሰጣጥ ፈቃዱን በነፃነት የሚገልፅበት ነፃ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ምርጫ፣ በገልተኝነት የሚያስ ፈዕም ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤
የተለያየ አመለካከት ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች የሚሳተፉበት እና አላማቸውን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመራጩ ህዝብ የሚገልፁበት መራጩ ህዝብ በመረጃ ላይ በመመስረት ፈቃዱን በነፃነት በመግለዕ ወኪሎቹን የሚመርጥበት የምርጫ ስርአት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በምርጫው ተሳታፊ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ የግል ዕጩዎች ለፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ስርአት መስፈን ገንቢ አስተዋጽኦ የሚያደርጉበት ግልፅ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በምርጫ ሂደት የሚከሰቱ አለመግባባቶች የሚፈቱበት የጋራ የምክክር መድረክና ሌሎች አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጡ ተቋማትን ማቋቋምና ቅሬታዎች በየደረጃው በይግባኝ የሚታዩበት ግልፅና ቀልጣፋ ስርአት መዘርጋት ተገቢ በመሆኑ፤
በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና አንቀጽ 102 መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•