የሀገራችን የማምረቻ፣ የንግድና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በቴክኒክና በሙያ ብቃት ያለው የሰለጠነ የሰው ኃይል ቀጥሮ በማሰራት ብቁ ተወዳዳሪና ዘላቂነት ያለው ድርጅታዊ አቋም እንዲ ኖራቸው ማስቻል አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ፤
ወጣቱ ትውልድ የሥነ-ልቦና ዝግጅት፣ የሥራ ዲስፒሊንና ችሎታ ያለው ብቁ ተቀጣሪና ሥራ ፈጣሪ እንዲሆን የሚያግዝ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት ማደራጀት በማስፈለጉ፤
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራም ብቃት ያለው የሰው ኃይል እንዲያዘጋጅ ሰልጣኞች ከመመረቃቸው በፊት በአምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ተሰማርተው የሥራ ልምምድ የሚያደርጉበት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ በመታመኑ፤
የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት ደረጃቸው የሚወሰንበትንና፣ ዕውቅና የሚያገኙበትን፣ እንዲሁም የሥልጠና ማጠናቀቂያና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የሚሰጥበትን ወጥነት ያለው ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የተሳካ እንዲሆን በፕሮግራም ቀረጻና በስርዓተ ትምህርቱ ዝግጅት፣ እንዲሁም በስልጠናው ግምገማና በአመራሩም ጭምር ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት የሚሳተፉበትን ሥርዓት ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 51 ንዑስ አንቀጽ (3) እና አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•