የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝቦች ሙስና እና ብልሹ አሠራር የአንድን አገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት የሚገታ ተግባር መሆኑን የተገነዘቡ በመሆናቸው፤
አገሪቱ የተያያዘችውን የእድገት ጎዳና እና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ለማፋጠንና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን በቁጥጥር ሥር ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ፣ ለዚህም ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመሸከም የማይፈልግ እና ይህንኑ በብቃት ለመዋጋት ዝግጁ የሆነ ሕብረተሰብ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤
ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለመመርመር፣ ለመክሰስ ለመቆጣጠርና ለመከላከል መልካም ሥነ ምግባር በኅብረተሰቡ ውስጥ እንዲስፋፋ በማድረግ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በብቃት መዋጋት እንዲቻል፣ የኮሚሽኑን አሰራርና እንቅስቃሴ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርሆዎችን በሚገልጽ መልኩ እንዲሁም ኮሚሽኑ ሀላፊነቱን በተሻለ ብቃት እንዲወጣ በሚያስችለው መልኩ የኮሚሽኑን ማቋቋሚያ አዋጅ ለማሻሻል በማስፈለጉ፤
የኮሚሽኑን ስልጣንና ተግባር ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ማሻሻል በማስፈለጉ፤
ኮሚሽኑ በከባድ የሙስና ወንጀሎች ላይ ትኩረት አድርጐ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ኮሚሽኑ ከሌሎች አግባብነት ካላቸው የምርመራና የአቃቤ ህግ ተቋማት ጋር ስለሚሰራበት ሁኔታ ዝርዝር ድንጋጌዎችን መደንገግ በማስፈለጉ፣
በሌሎችም ግልጽነት በሚያንሳቸው አንዳንድ የአዋጁ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያዎችን ማድረግ በማስፈለጉ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል።
•