የወንጀል ድርጊቶች ከተፈጸሙ በኋላ ፈጻሚዎቹ ተደብቀው እንዳይቀሩና ህግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ በማድረግ የህብረተሰቡ ሰላማዊ ኑሮ የሚረጋገጥበትን ሁኔታ ማመቻቸት አስፈላጊ በመሆኑ፤
ለወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ መስጠት በኅብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ስጋት ሊያስከትሉ የሚችሉ ወንጀሎችን በማጋለጥ ወንጀልን ለመከላ ከል የሚረዳ በመሆኑ፤
የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች በምስክርነታቸው ወይም በጠቋሚነታቸው ምክንያት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ከሚደርስባቸው አደጋና ጥቃት ለመከላከልና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የጥበቃ ሥርአቶችን በሕግ መደንገግ በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•