የማኅበራዊ ዋስትናን ሥርዓት በማስፋፋት ደረጃ በደረጃ ለዜጎች እንዲደርስ ማድረግ ከሀገሪቱ ማኅበራዊ ፖሊሲ አንዱ አካል በመሆኑ፤
የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድን እና ፈንድን በማሻሻልና በማጠናከር ዘላቂነትና አስተማማኝነቱን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤
በሀገሪቱ እየታየ ካለው ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት ጋር የተጣጣመና ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋትና አሠራሩን ማዘመን ስለሚገባ፤
የሥርዓቱ መስፋፋትና ተጠናክሮ መቀጠል ለማኅበራዊ ፍትሕ፣ ለኢንዱስትሪ ሰላም፣ ለድህነት ቅነሳና ለልማት ጉልህ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡