የማህበራዊ ዋስትናን ስርዓት በማስፋፋት ደረጃ በደረጃ ለዜጎች እንዲዳረስ ማድረግ ከአገሪቷ ማህበራዊ ፖሊሲ አንዱ አካል በመሆኑ፤
የስርዓቱ መስፋፋትና ተጠናክሮ መቀጠል ለማህበራዊ ፍትሕ፣ ለኢንዱስትሪ ሰላም፣ ለድህነት ቅነሳና ለልማት ጉልህ አስተዋፆ ስለሚኖረው፤
የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ ዐቅድ እንዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•