በአገልግሎት ላይ

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት እንዲሁም ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች የተረጋገጠውን የመደራጀት መብት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤

የመደራጀት መብት በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡ ሌሎች መብቶችን ለማስከበር ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ፤

በሕገ መንግሥቱ እንደተደነገገው፣ የመንግሥት አሠራር በግልጽነት፣በተጠያቂነትና በአሳታፊነት እንዲከናወን ለማድረግ የነቃና በነፃነት የተደራጀ ማኅበረሰብ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን በማመን፤

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአገሪቱ ልማትና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላቸው ሚና እንዲጎለብት ለማድረግ የተመቻቸ ምህዳር መፍጠር ወሳኝ መሆኑን በመረዳት፤

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ተጠያቂነት እና የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ድርጅቶቹ ሥራቸውን በሕግ መሠረት መሥራታቸውን መቆጣጠር በማስፈለጉ፤

በሕብረተሰቡ ዘንድ የበጎ አድራጎት እና የበጎ ፈቃደኝነት ባሕልና እንዲዳብር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማመን፤

ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በሥራ ላይ የነበረው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 የነበሩበትን ክፍተቶች ለመሸፈን የሚያስችል አዲስ ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

 

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1113/2011
ቀን: መጋቢት 03፥ 2011 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

ደንብ ቁጥር 168/2001

ጥቅምት 30፥ 2002 ዓ.ም.
የተሻረ
አዋጅ ቁጥር 621/2001

የካቲት 6፥ 2001 ዓ.ም.
የተሻረ