ለአርባረከቲ-ገለምሶ-ሚቸታ የመንገድ ሥራ ማሻሻያ ፕሮጀክት ክፍል 2፡- ገለምሶ-ሚቸታ ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 23 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (ሃያ ሦስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በኦፔክ ፈንድ ለዓለም አቀፍ ልማት መካከል እ.አ.አ. ኤፕሪል 12 ቀን 2014 ዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡