የተሻረ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ (ማሻሻያ) አዋጅ

የኦዲት ሥርዓትን ማጠናከር መንግሥት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በሚገባ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚያስፈልገው አስተማማኝ መረጃ በማግኘት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ፤

በልዩ ልዩ የልማትና አስተዳደር መስኮች የተሰማሩ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች የገንዘብ አስተዳደር ተገቢውን የሂሣብ አያያዝ ሥርዓት የተከተለ፣ የገቢ አሰባሰባቸው፣ የወጪ አፈቃቀዳቸውና የንብረት አስተዳደራቸው የመንግሥት ሕግንና መመሪያን ተከትሎ የተፈጸመ መሆኑንና ዕቅድና ፕሮግራማቸውንም በቅልጥፍና እና ኢኮኖሚያዊ በሆነ መንገድ በማከናወን የሚጠበቅባቸውን ግብ ማሟላታቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በሚገኙ ልዩ ልዩ የፌዴራሉ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ተጠያቂነትን፣ ግልጽነትን እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ኦዲት ዓይነተኛ መሣሪያ በመሆኑ፤

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲን በሚገባ ተግባራዊ ማድረግ ይቻል ዘንድ በፌዴራላዊ መንግሥት ይዞታ ሥር የሚገኙ የአስተዳደር፣ የልማትና የአገልግሎት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች በብቃት ለመቆጣጠር በተጠናከረና ዘመናዊ በሆነ የኦዲት ተግባር መታገዝ ያለበት በመሆኑ፤

ለዚህ ተግባራዊነት በቅርቡ የተካሔደው የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት የፌዴራል ዋና ኦዲተሩንና የመሥሪያ ቤቱን የሙያ ነፃነትና አሰራር ይበልጥ ማሻሻልና ማጠናከር እንደሚገባ ማመልከቱ በመረጋገጡ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55 መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 669/2002
ቀን: ግንቦት 3፥ 2002 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

No data was found