በአገልግሎት ላይ

የማሪታይም ዘርፍ አስተዳደር አዋጅን ማፅደቂያ አዋጅ

የተቀላጠፈ የማሪታይም ዘርፍ አገልግሎት ለአገር ልማትና ብልጽግና እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ በተፋጠነ ሁኔታ ተሻሽሎና በተቀናጀ አደረጃጀት ተስፋፍቶ የበለጠና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ በማስፈለጉ፤

በዘመናዊ የአሠራር ቴክኒክ ዘዴዎች በመጠቀም የደረቅ ወደቦችን፣ የባሕር ማመላለሻንና መልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎትን መጠቀም እንዲቻል ለማድረግ፣ መርከቦችን፣ የባሕር ጉዞዎችንና ሌሎች የማሪታይም ዘርፍ አገልግሎቶችን በሚገባ መምራትና መቆጣጠር አስፈላጊ በመሆኑ፣ እንዲሁም የአገር ውስጥ የውሃ ኃብትን ለበለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲውል ለማድረግ፣እና

በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ሥር ተበታትነው ያሉትን ተግባራት በአንድ ላይ በማሰባሰብ በማሪታይም ዘርፍ የሚከሰቱ ችግሮችን ተከታትሎ መፍትሔ የሚሰጥ፣ በአለም ዓቀፍ ባሕር ስምምነቶች ላይ በመመስረት አገራችን ግዴታዋን እንድትወጣ እና ልታገኝ የሚገባትንም ጥቅሞች ተከታትሎ በባለቤትነት የሚያስፈጽም ለትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር በቀጥታ ተጠሪ የሆነ መንግሥታዊ አካል ማቋቋም በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 549/1999
ቀን: ነሐሴ 29፥ 1999 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

ደንብ ቁጥር 454/2012

መስከረም 15፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 274/2005

ታህሳስ 1፥ 2005 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ