የአገሪቱን የኢኮኖሚ ልማት ለማፋጠንና የሕዝቦቿን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ኢንቨስትመንትን በተለይም የማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍን በማበረታታትና በማስፋፋት የአገር ውስጥ የማምረት አቅምን ማጠናከር በማስፈለጉ፤
ወደ አገር ውስጥ የሚገባውን የካፒታል ፍሰት ይበልጥ ማሳደግና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን በማስፈለጉ፤
የኢንቨስትመንት ክልላዊ ሥርጭትን ማሻሻልና በሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች መካከል ውድድርን በማስፈን ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ በማስፈለጉ፤
ለባለሀብቶች የሚሰጡ ፈቃዶችና ማበረታቻዎች ለታለመላቸው ዓላማዎች በአግባቡ መዋላቸውን ማረጋገጥ የሚያስችል የክትትል ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
ኢንቨስትመንት የሚመራበት ሥርዓት በይበልጥ ግልጽና ቀልጣፋ አንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፤
የኢንዱስትሪ ልማት ቀጠናዎች መቋቋም ምቹና ተወዳዳሪ ከባቢያዊ ሁኔታዎችን በመፍጠር የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች አርስ በርስ ተመጋግበውና በእሴት ሰንሰለት ተሳስረው የሚያድጉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ኢንቨስትመንትን በመሣብና በማስፋፋት ረገድ አይነተኛ መንገድ መሆኑ ስለታመነበት፤
አነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ በሥራ ላይ ያለውን የኢንቨስትመንት ሕግ ማሻሻል አስፈሳጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•