ለሦስተኛው የአርብቶ አደር አካባቢዎች ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 55 ሚሊዮን 300 ሺህ ኤስ.ዲ.አር (ሃምሳ አምስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዓለም ዓቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል እ.አ.አ ዲሴምበር 16 ቀን 2013 በሮም የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 25 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡