ለሦስተኛው የአርብቶ አደር አካባቢዎች ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 71 ሚሊዮን 800 ሺህ ኤስ.ዲ.አር (ሰባ አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር መካከል እ.አ.አ ጃንዋሪ 16 ቀን 2014 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 25 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡