የአገሪቱን የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽንና ልማትን ሊያፋጥኑ የሚችሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በተመረጡ አካባቢዎች በማቋቋም ውጤታማ የአገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ኢንዱስትሪዎችን ማሳደግና ተዛማጅ የስራ እድል መፍጠር በማስፈለጉ፤
የኤክስፖርት ልማት ማሳደግን፣ የአካባቢና የሰው ደኅንነት መጠበቅን እና በቁጠባ መሬት መጠቀምን እንዲሁም የከተሞች ዕድገት በዕቅድና በስርዓት የመምራትን አስፈላጊነት በመገንዘብ፤
የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማቋቋም፣ የአሰራር፣ የልማት፣ የአስተዳደር እና የቁጥጥር ስርዓትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመለከት የሕግ ማዕቀፍ ማውጣት ያለውን ከፍተኛ ጠቃሜታ በመረዳት፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•