ለድሬዳዋ-ደወሌ መንገድ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 187 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል እ.አ.አ ሜይ 4 ቀን 2014 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡