የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመከላከያ ሠራዊት የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር፣ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ እና ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በመሆን ተግባሩን እንዲያከናውን የተደራጀ መሆኑ፤
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመከላከያ ሠራዊት የሚመራበትን እና ከተቋሙ ወቅታዊ ግዳጅ ጋር የሚጣጣም እንዲሁም የወደፊቱን ግዳጅ ታሳቢ ያደረገ የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ፤
በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመከላከያ ሠራዊት የህግ ማዕቀፍ ማሻሻልና ማጠቃለል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•