ኢትዮጵያ እኤአ የ1978 የኤስቲሲ ደብሊው ኮንቬንሽን (STCW Convention) አባል ስለሆነች፤
ኢትዮጵያ የ1978 ኮንቬሽንና ይህንኑ ኮንቬሽን ያሻሻለውን የ1995 ኮንቬሽን ስለተቀበለች ይህንኑ የተሻሻለ ኮንቬሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 17 ቀን 1995 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።