በአገልግሎት ላይ

የኢትዮጵያ ፊዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጋራ ህንፃ ቤት ባለቤትነት አዋጅ

በከተሞች ያለውን የቤት አቅርቦትና የቤት ፍላጐት አለመጣጣም ለመቀነስ የከተማ ቦታን በግል ከመሸንሸን በተጨማሪ ሌሎች የከተማ ቦታ አጠቃቀም አማራጮችን ጐን ለጐን ተግባራዊማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፤

የከተማ ቦታን ወደ ላይ ወይም ጐን ለጐን የተሠሩ ቤቶችን ለሚይዝ የጋራ ሕንፃ ግንባታ ማዋል አነስተኛ የከተማ ቦታ የብዙ ሰዎች የጋራ ይዞታ እና መጠቀሚያ እንዲሆን በማድረግ የከተማ ቦታ አጠቃቀምንና የቤት አቅርቦትን በማሻሻል እንዲሁም የከተሞችን ውበት በመጠበቅ ረገድ የሚኖረውን ድርሻ በመረዳት፤

የግል አልሚዎችና የኅብረት ስራ ማኅበራት በጋራ ሕንጻ ግንባታ ለሚኖራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና የጋራ ሕንጻ ቤት ለሚገዙ ወይም ለሌሎች በጋራ ሕንጻው ላይ ባለመብት ለሆኑ ሰዎችምቹ ሁኔታ መፍጠር ለጋራ ሕንጻ ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ፤

ለዚህም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) በተደነገገው መሠረት ይህ አዋጅ ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 370/1995
ቀን: ጳጉሜ 6፥ 1995 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

No data was found