በነጻ ገበያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረት በማናቸውም የንግድ ሥራ መስክ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር አስፈላጊ ስለሆነ፤
የንግድ ሥራ ፈቃድ አሰጣጥና የምዝገባ ሥርዓት የነጻ ገበያ ኢኮኖሚን ለማራመድ በሚያስችል መልኩ እንዲሻሻል ማድረግና ሕጋዊ ሆኖ የተሰማራው ኅብረተሰብ በዚህ ረገድ የሚያጋጥሙትን መሰናክሎች ማስወገድ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ፤
በአንድ በኩል ለሕጋዊ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ተገቢ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን መግታት አስፈላጊ ስለሚሆን፤
እስከአሁን በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በተበታተነ ሁኔታ ሲከናወን የነበረውን የንግድ ሥራ ፈቃድ የመስጠት ተግባር በሥራዎቹ ልዩ ባህርይ ምክንያት በሌላ መሥሪያ ቤት እንዲሰጡ የግድ አስፈላጊ ከሆኑት በስተቀር ለአፈጻጸም በሚያመችና ከሞላ ጐደል በተጠቃለለ መልክ አግባብ ባላቸው የንግድና ኢንዱስትሪ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ብቻ መከናወን እንዳለበት ስለታመነበት፤
ቀደም ሲል ለነበሩ ሥርዓቶች እንዲያገለግሉ ተቀርጸው እስከ አሁን በሥራ ላይ የሚገኙ ሕጐች አንዳንድ ድንጋጌዎች በአሁኑ ወቅት ከምናራምደው የነጻ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት ጋር ስለማይ ጣጣሙ አስፈላጊውን ለውጥ ማድረግ ተገቢ ስለሆነና በተለያዩ አዋጆች ተበታትነው የሚገኙትን የምዝገባና የፈቃድ አሰጣጥ ድንጋጌዎች በአንድ አዋጅ አጠቃሎ ማውጣት አስፈላጊ ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ–መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•