ካፒታል በማሰባሰብ፣ የገንዘብ ስርዓቱን በአዳዲስ ፈጠራዎች በመደገፍ እና የኢንቨስትመንት ስጋቶችን የመጋራት አሰራርን በማስፋፋት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ልማት የሚደግፍ የካፒታል ገበያ ማቋቋም በማስፈለጉ፤
ኢንቨስተሮችን ለመጠበቅ እና ገበያው ፍትሃዊ፣ ተአማኒ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የሚያስችል የቁጥጥር እና በበላይነት የመከታተል የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በማስፈለጉ፤
ከሕዝብ ካፒታል ለመሰብሰብ የሚፈልጉ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች የሚገዙበትን ወጥ የሆኑ መስፈርቶች በህግ መደንገግ በማስፈለጉ፤
በሀገሪቱ : የፋይናንስ ስርዓት ላይ የሚፈጠሩ መዋቅራዊ ስጋቶችን ለመለየት፣ ለመከላከል፣ እና ለመቀነስ በካፒታል ገበያ ላይ ጠንካራ የቅርብ ክትትል እና የቅኝት ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው አዋጅ ታውጇል፡፡
•