የተሻረ

ባንክ ሥራ አዋጅ

ባንኮች ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር ገንዘብ በማሰባሰብ በተለያዩ የልማት ዘርፎች እንዲውል በማድረግ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው፤

ባንኮች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ የክፍያና የክፍያ አፈጻጸም ሥርዓት ውስጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው በመሆናቸው፣

የባንክ ሥራ በተገቢው ሥርዓት አለመመራት በፋይናንስ ሥርዓቱና በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ ጎጂ የሆነ ያለመረጋጋት ሁኔታን የማስከተል ባህሪያት ያሉት በመሆኑ፤

በፋይናንስ ሥርዓቱና በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ የሚደርሰው አለመረጋጋት በሕዝብና በመንግሥት ላይ የሚያስከትለውም ጉዳት በቀላሉ የሚገመት ባለመሆኑ፤

የባንክ ሥራ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥርን በሚመለከት ሁለአቀፍ ሕግ በማውጣት የባንክ ሥርዓቱ ለአደጋ ያልተጋለጠ፣ አስተማማኝና የተረጋጋ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 592/2000
ቀን: ነሐሴ 19፥ 2000 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

No data was found