በአገር እና በአለም አቀፍ ደረጃ በሰዎች መካከል የሚደረጉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች መስተጋብሮችን በሚመለከት የሚፈፀሙ የውል እና ሌሎች ግንኙነቶችን በሕግ አግባብ በማረጋገጥ እምነት የሚጣልበት ሰነድ በማመንጨት እንዲሁም ሰነዶችን መዝግቦ በመያዝ በማናቸውም ጊዜ እንዲገኙ በማድረግ ለሕገ-መንግስታዊ መብቶች ዋስትና መስጠት በማስፈለጉ፤
የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ተግባር በመላ አገሪቱ ወጥ የሆነ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ፣ አገር አቀፍና አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አሰራር እንዲኖረው የሚያስችል ሕግ በማስፈለጉ፤
በሰነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ተቋማት መካከል ግልጽ ግንኙነት የሚፈጥር እና ያለአግባብ የሚረጋገጡ ሰነዶችን መቆጣጠር የሚያስችል የተሻሻለ ሥርዓት መኖሩ በሰዎች መካከል የሚደረጉ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ግንኙነቶችን በማቀላጠፍ እንዲሁም አሰራሩን ተገማች በማድረግ በሀገሪቱ ውስጥ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር የበለጠ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ እና እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ በሥራ ላይ ያሉትን የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ ሕጎች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግስት አንቀጽ 55 (6) መሠረት ከዚህ የሚከተለው ታውጇል፡፡